free book gift

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።


Iqra

=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=

ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ


1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።

2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።

3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።

4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
Iqra
Iqra

Homeየወጣቱ ተልዕኮ ምንነትየአቂዳ ትምህርቶችየሶላት መመሪያረመዷንሙስሊም ሴቶችኢስላማዊ ቤተሰብከታሪክ ማህደርሐዲስለወጣቶችትምህርትና መሰረታዊ ክህሎታችጤናችንግጥምጥያቄና መልስኢስላማዊ መዝገበ ቃላት
free book gift

=<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=

ያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም አንብብ!

free book gift

በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።

free book gift

:☀:♥ 10 ግቦች ለወጣት እህት ወንድሞቼ ♥:☀:


FemaleMuslimstudentswalktoschoolinKotaBharuKelantanMalaysiaSept.102009.PhotographerGohSengChongBloomberg

1) ሃቀኛ እንሁን

በዚህ የውድድር እና እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ በሚል ማህበረሰብ ውስጥ ለወጣቶች ሃቀኛ(እውነትን ተናጋሪ) መሆን አስቸጋሪና ፈታኝ ነገር ሊሆን ይችላል።

አብዛሃኛዎቻችን ጥፋት ስናጠፋ ቤተሰቦቻችን ፣ አስተማሪዎቻችን ፣ ጓደኛዎቻችን ይርቁናል ፣ ይጠሉናል ፣ በኛ ላይ መጥፎ አመለካከት ይኖራቸዋል በማለት አብዛሃኛውን ጊዜ እንዋሻለን። ምሳሌ:- የቤት ስራችነን ካልሰራን ከመቀጣት ለመዳን ስንል ውሸትን እንፈበርካለን፤ እንዲሁም አንድ ጥፋት ካጠፋን እውነቱን ከቤተሰቦቻችን እንሸሽጋለን። ሃቀኛ ለመሆን ካሰብን ከሃጢያቶች መራቅ ይኖርብናል። የቤት ስራችነን በሰዓቱ ከሰራን ውሸት መናገርን ማስወገድ እንችላለን። በዚህም ሆነ በመጭው አለም ታላቅ የሆነ ስኬትም እንጐናፀፋለን።


-<({አል-ቁርአን 5:119-120})>-

(119) «አሏህም ይላል:- ይህ ቀንነው ሃቀኞች በሃቀኝነታቸው የሚጠቀሙት ከስራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው የሆኑ ጀነቶች አሏቸው። በውስጣቸውም ለዘላለም ይኖራሉ። አሏህ ከነሱ ወደደ፤ እነርሱም ከአሏህ ወደዱ። ይህ ታላቅ ስኬት ነው።

(120) በሰማያትና በምድር በውስጣቸውም ያለ ሁሉ ንግስና የአሏህ ብቻ ነው። እሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው።»

በቡሐሪ እንደተዘገበው አብዱሏህ(ረ.ዐ) እንደተረከው ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል: እውነተኛ ሰው እውነትን በመናገር ላይ እስከ ቀጠለ ድረስ ሃቀኝኝነት ወደ ቅድስና ይመራል ቅድስና ደግሞ ወደ ጀነት ይመራል። ውሸተኝነት ወደ እርጉምነት(ክፋት) ሲያመራ እርጉምነት(ክፋት) ወደ ጀሃነም ያመራል።


2) ለቤተሰቦቻችን ደግ እንሁን

እኛ ወጣቶች የራሳችነን ስሜት ተከትለን ለመኖር ስንል ቤተሰቦቻችን በሂወታችን ጣልቃ እንዳይገቡ በማሰብ እነሱን እንቃረናለን፤ ምክራቸውንም እናጣጥላለን። ቤተሰቦቻችን ለዛሬው ማንነታችን የጧት ጮራ ናቸው። ለኛ የማያልሙትና የማይደክሙት ድካም የለም። ህልማቸው እውን ሆኖ ማየት ይሻሉ። እኛ ያላየነውን ስንት ድካምና ችግር ፣ መከራ ገጥሟቸዋል። ለቤተሰቦቻችን ደግ እንሁን ለእያንዳንዱ ለምንሰራቸው ስራዎች ምክራቸውን እንሻ።


-<({አል-ቁርአን 31:14})>-

«ሰውንም ለቤተሰቦቹ በጎ ነገርን እንዲያደርግ በጥብቅ አዘዝነው። እናቱ ከድካም በላይ በሆነ ድካም አረገዘችው። ጡት መጣያውም በሁለት አመት ውስጥ ነው። ለኔም ለወላጆችህም አመስግን በማለት አዘዝነው። መመለሻውም ወደ ኔ ነው።»


3) ሶብር(ትዕግስት) እና እራስን የመቆጣጠር ብቃቱ ይኑረን

አልኮል መጠጥ ከጏደኞቻችን ጋር መጠጣትን እንሻለን እንዴ? አልኮል መጠጣት በኢስላም ሐራም መሆኑን እናውቃለን። ታዲያ ይህን እያወቅን እንዴት በአሉቧልታ ህግጋቱን እንጥሳለን። ለአሏ የትም ቦታ እንሁን አሏህ የምንሰራውን ሁሉ ሰሚም ተመልካች መሆኑን አውቀን እራሳችነን እንቆጣጠር።

ሴቶችን ወይም ወንዶችን በትምህርት ቤታችን ፣ በየዩኒቨርስቲው ፣ በፌስብክ ማየትን እንሻለን እንዴ? እውነት እንደዚህ አይነት አባዜ ካለብን በቁርአንና በሐዲስ ያሉ ህግጋቶችን እየጣስን መሆናችነን አንዘንጋ!!!


-<({አል-ቁርአን 41:35-36})>-

(35) «ይህችንም ፀባይ ማንም አያገኛትም፤ እነዚያ የታገሱትና የትልቅ እድልም ባለቤት የሆኑት ሲቀሩ።

(36) ከሰይጣንም ጉትጎታ ቢያጋጥምህ፤ ከመልካም ፀባይም ቢመልስህ በአሏህ ተጠበቅ። እነሆ እርሱ አሏህ ሁሉን ሰሚ ሁሉን አዋቂ ነውና።»


4) ለምንሰራው ስራ ትኩረት እንስጥ

አብዛሃኛውን ጊዜ እኛ ወጣቶች ለምንሰራው ስራ ትኩረትን አንሰጥም። ረጋ ብሎ ከመስራት ይልቅ ነገራቶችን አቻኩለንና ነካ ነካ አድርገን ሰርተን እናልፋቸዋለን። ትምህርት ቤት ከገባን ጀምሮ የተወሰኑ መጽሐፎችን አንብበናል፤ ነገር ግን ንባባችን አትኩሮት የጐደለው ስለሆነ በእያንዳንዱ የክፍል ደረጃ በቂና ተፈላጊውን እውቀት ይዘን መውጣት አልቻልንም። ትእግስተኞችና ለስራቸው አትኩሮት የሚሰጡት ሲቀሩ።

ትንሽ አንብበን ብዙ መረዳትና ማብላላት ስንችል ብዙ ጊዜያችነን አቃጥለን ትንሽ እንረዳለን። ሰዎች መልዕክት አድርሱ ብለውን መልዕክቱ ይጠፋብናል ወይም ያልሆነ መልዕክት ተናግረን ችግር ይፈጠራል። ቤተሰቦቻችን ሱቅ ልከውን ያልሆነ ነገር ገዝተን እንመጣለን። ለዚህ ሁሉ ችግር ምክኒያቱ ለምንሰራው ስራ ትኩረት አለመስጠታቸን ነው። ለዚህም ዋናው መፍትሄ ሶላታችንን ስንሰግድ ምስጥ ብለን በሙሉ አትኩሮት መስገድ ነው። እናም ለሌሎች ለምንሰራቸው ስራዎች አትኩሮት ይኖረናል ማለት ነው።


-<({አል-ቁርአን 23:9-11})>-

(9) «እነዚያ ሶላቶቻቸውን በጥንቃቄ የሚጠብቁ የሆኑ (አገኙ)።

(10) በእርግጥ እነሱ ወራሰሾች ናቸው።

(11) እነርሱ የፊርደውስ ወራሾች ናቸው። በውስጧም ለዘላለም ይኖራሉ።»

-<({አል-ቁርአን 31:17})>-

«ልጄ ሆይ! ሶላትን አስተካክለህ ስገድ በመልካም ነገር እዘዝ፤ ከመጥፎ ነገር ሁሉ ከልክል፤ በሚያገኝህም መከራ ላይ ታገስ። ይህም በምር ከሚያዙ ነገሮች ነው።»


5) ቆራጥ እንሁን

አንድ ሰው ለምንድ ነው የምትማሩት? ብሎ ቢጠይቀን ማንኛውም ሰው እንደሚማረው ነው የምማረው እንላለን እንዴ? አንልም። ምክኒያቱም ይህ መልስ ደካማነታችነን ያመላክታን። ቆራጥነት በጣም ጠቃሚ ነው። በአላማችን ቆራጥ ካልሆን ወዴት እንደምንሄድና ሂወታችን ምን ላይ እንደሆነ ማወቅ አንችልም። ሁሉም ስራዎቻችን ከትምህርት ቤት እስከ ሶላቶቻችን ያሉ ስራዎች ባዶና ብልጭልጭ ብቻ ነው የሚሆኑት። ስኬታማ ለመሆን ወሳኙና አስፈላጊው ነገር ቆራጥነታችን ነው።

6) የማይረባ እንቶፈንቶ ወግ እናስወግድ

የማይረባ ወግ ወጣቶች ላይ በሰፊው ይስተዋላል። አብዛሃኛውን ጊዜ ስለምን እንደምናወጋ እንኴ አናውቅም። አስፈላጊ ያልሆኑ ማለትም ነሽዳ ተብሎ ሙዚቃ የሆኑ ባዶ ወሬዎችን ፣ ፊልሞችን ፣ የእግርኴስ ጨዋታ ወ.ዘ.ተ እራሳችነን ተሳታፊ እናደርጋለን። ይህ ደግሞ ከትክክለኛው መንገድ ሊያስወጣን እንደሚችል ልናውቅ ይገባል። የመማራችን ወይም ሌላን ስራ የመስራታችን አላማ አጠያያቂ ይሆናል። መልካም ሃሳባችን አደጋ ውስጥ ይገባል። የምንቸገረው በዚህ አለም ብቻ ሳይሆን በመጭው አለም ጭምር ነው። ስለዚህ ከእንቶፈንቶ ወግ እንራቅ የአሉቧልታ ወግ ስራዎቻችነን ሁሉ ያበላሻልና!!!

7) አለማዊ ለሆኑ ነገሮች ምርኮኞች አንሁን

አብዛሃኛዎቻችን ለመጭው አለም አንጨነቅም። እማንሞት የሚመስለንም አንጠፋም። እናም በማንኛውም ነገር ለመደሰት አለማችነን ለመቅጨት የቻልነውን ሁሉ እንሞክራለን። አሏህ የምንሰራቸውን ሰራዎች ተመልካች መሆኑን ዘንግተናል! አሏህ በደነገገው መሠረት ሂወታችነን የምንመራ ከሆነና በወጣትነታችን ስሜታችነን ተቆጣጥረን ለአሏህ ትዕዛዝ እራሳችነን ተገዥ ካደረግን በዚህም ሆነ በመጭው አለም አሸናፊዎች እንሆናለን!!!


-<({አል-ቁርአን 31:33})>-


«የሰው ልጆች ሆይ! ጌታችሁን ፍሩ፤ አባት ልጁን የማይጠቅምበት ፣ ልጁም አባቱን የማይጠቅምበት የሆነችን ቀን ፍሩ። በእርግጥ የአሏህ ቃልኪዳን እውነት ነው። እናም የዱንያ ሂወት አታሞኛችሁ። በአታላዩ ሸይጧን ስለ አሏህ አትታለሉ።»


8) ጊዜያችነን እና ገንዘባችነን ባረባ ነገር አናባክን

ሱብሃን አሏህ! ይህ የረሱል ኡማ ለጀሂልያው ዘመን ብርሃን የሆኑትን ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ካገኘ ቡኋላ ዳግም ወደ ጃሂልያ ዘመን መመለስን የሚሻ ይመስላል። በዚህም ላይ ልባችን የከዳን ወጣቶች በfacebook ላይ ያለን ተግባር(ፖስት የምናደርገው ፣ ላይክና ኮሜንት የምንሰጠው) ነገር ሁሉ ህያው ምስክር ነው። አጂብ ነው! 3ሰዓት ሙሉ facebook ላይ ነን ፖስት የምናደርገው ፣ ላይክና ኮሜንት የምንሰጠው እንዲሁም ቻት የምናደርግበት መሠረተ ሃሳብ ባዶ ነው። 3ሰዓት ሙሉ ለዲናችን ጊዜ የሰጠን ሙሉ 3ሰዓት ቁርአን በመቅራት ፣ ኢልምን በመሻት ጊዜያችንን የምናሳልፍ ስንቶቻችን እንሆን? ጊዜያችን እና ገንዘባችን እኛን መጥቀም ካልቻለ እኛም በሱ ላይ መጠቀም ካልቻልን ታዲያ መዳረሻችን ወዴት ሊሆን እንደሚችል አናስብም እንዴ? ስለዚህ ውድ ሙስሊም እህት ወንድሞቼ አይደለም ጊዜያችንን በእንቶፈንቶ ወግ አሳልፈነው ቀርቶ አሏህን በመገዛት ብናሳልፈው እንኴ በቂ አይደለም። ስለዚህ ከእንደዚህ አይነት እርካሽ ተግባር እንውጣ። ጊዜው ሳይጨልምብን የሞትን ፈተና ከመቅመሳችን በፊት ወደ አሏህ እንመለስ።


-<({አልቁርአን 7:31})>-

<<የአደም ልጆች ሆይ!.....ብሉም ጠጡም አታባክኑም፤ አሏህ አባካኞችን አይወድምና።>>

10) የአሏህ ፍራቻ በልባችን ውስጥ ይኑረን

ትክክለኛ ሙዕሚን እና አሏህን ፈሪዎች ከሆን ከላይ የተዘረዘሩትን ባህሪያቶች ይኖሩናል። ሁል ጊዜም አሏህ እያየን መሆኑን የምናውቅ አሏህን ፈሪዎች ብንሆን ኖሮ ቤተሰቦቻችነን አገልጋዮች ፣ ለዋሉልን ውለታም አመስጋኞች ፣ እውነታኛና ታማኝ በሆን ነበር።

ውድ ሙስሊም እህት ወንድሞቼ መኖራችን በኢስላም ህግጋት ይሁን። አሏህ ባህሪያቸውና ተግባራቸው ከተስተካከሉት ባሮቹ መካከል ያድርገን። አሏህ መጨረሻችነንም አሏህ ያሳምርልን!!!

Websites:
http://youth-mission.mobie.in

http://youth-mission.blogspot.com

fb page:
http://facebook.com/youth.mission29

© ዝግጅት በአህመድ የሱፍ
2006

1490

የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
free book gift

Download Islamic Books
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ

Important Web Links


free book gift

free book gift

free book gift

ስለወጣቱ ተልዕኮ ምንነት ለማወቅ እዚህ ላይ ክሊክ ያድርጉ

Copyright©Youth-Mission የወጣቱ ተልዕኮ


Polaroid